ጥር ፫ (ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ቁጥራቸው በውል ባይታወቅም ከ 20 ያላነሱ ሰዎች ታስረው ወደ አልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል።
አብዛኞቹ ወጣቶች ወደ ማይጨው እስር ቤት ተወስደው መታሰራቸው ታውቋል። ከታሰሩት መካከል አቶ አባተ ያለው እስከ ልጃቸው፣ አቶ አሰፋ ዳርጎ ከሴት ልጃቸው ጋር ፣ ሽበሺ አለሙ፣ አሰፋ አሰግድ ፣ ውዱ ቸኮል፣ አቶ ዝናቡ ቸኮል ከሴት ልጃቸው ጋር እንዲሁም አቶ ፋንታ መሰለ ይገኙበታል። አቶ ፋንታው መሰለ እና ሌሎች ሶስት ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም።
በርካታ የአካባቢው ወጣቶች ወደ ተለያዩ አካባቢዎች መሄዳቸው ታውቋል።
በኦስትሪያ ዜጋ ላይ ግድያ ፈጽመዋል ተብለው ከተረጠሩት መካከል ሁለቱ መያዛቸውን መንግስት አስታወቀ
ጥር ፫ (ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ባወጣው መግለጫ እንደጠቀሰው ተጠርጣሪዎቹ በአማራ ክልል የጸጥታ ሀይሎች አማካኝነት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል።
ወንጀሉ ተራ የዘረፋ ሙከራ መሆኑን መንግስት ይናገራል። አንዳንድ ተቃዋሚዎች በበኩላቸው ድርጊቱን መፈጸማቸውን ይናገራሉ።
የሟቹ አስከሬን ከትናንት በስቲያ ወደ ሀገሩ መላኩ ታውቋል።
No comments:
Post a Comment