(በ ይግዛው እ.)
ማንአለብኝ ብለው በመግደል ተለክፈው
ሰውን እያጠፉ ሊኖሩ ፈልገው
ዛሬም ስደት ቦታ በዘር ተደራጅተው
ልክ ነን ይላሉ በግልጽ አፍ አውጥተው::
ያሉበትን እንኳ በውል ያልተረዱ
በጫካ አስተሳሰብ እስካሁን ሚነጉዱ
በአንድ ዘር መነጽር ሰዎችን እያዩ
ከተቃወሙአችው እንግደል ይላሉ::
ጥፋቱን የማያውቅ የሀገር ነቀርሳ
ጌታቸውን አርገው ሁሌ ማይነሳ
ይመጻደቃሉ በያሉበት ሆነው
አይዞህ ያሏቸውን ጌቶቹን ተማምነው::
ወያኔ አሜሪካ ሌላው በአረብ አገር
ከመሞት መሰንበት ተሰደን በኖርን
የደላን መስሏቸው የስደት ኑሮአችን
ይከታተሉናል ከዚህም ሊአጠፉን::
ስደተኞች ሁሉ ታግለን ለውጥ እናምጣ
ከህዝብ ጎን እንቁም ማንም ለእኛ አይመጣ::
አውሮፓ አሜሪካ UN ን አንጠብቅ
ባለን ጀምረን ሲያልቅብን እንጠይቅ::
ተገፍተን ተገፍተን ተንጠን ተንጠን
መከራው ሲበዛ ግዞት በቃ ብለን
ይህን ያገር ጠላት ቁመን ካልታገልን
በተራ ለመሞት ቀን እየጠበቅን
እስከመቸ እንተኛ ይህን ስጋ ወደን::
ለጊዜው ቢመስለን ቁመን ምንራመድ
ወጥተን ማንገባበት ተዘርግቷል ወጥመድ::
ከእኛው ሀብት ተሰደን በእኛው ሀብት ሊገሉን
ብር እያነጠፉ አዚህ ሲከተሉን
ዝም በለን ካየን ካልቆምን ለመብታችን
ማርስም ላይ ብንወጣ አይቀርም ሞታችን::
ጎበዝ ባለህበት ምከር ተሰናዳ
ብድርህን አስከፍል የወያኔን እዳ::
No comments:
Post a Comment