FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS
Wednesday, December 19, 2012
የእስክንድር ነጋ የዛሬ የፍርድ ቤት ውሎ........የእስክንድር የመከራከሪያ መልሶች
እስክንድር የይግባኝ መከራከሪያ ነጥቦቹን ራሱ ነበር ያቀረበው
እስኪ እንመልከተው
እስክንድር ላይ የቀረበ የአቃቤ ህግ የክስ ጭብጥ በኢፊድሪ ሕገ-መንግስት መሠረት በአመፅ ያለምርጫ ስልጣን መያዝ ኢ-ሕገ መንግስቲዊ ድርጊት ነው፡፡ይህንንም ከግብ ለማድረስ
1 -የArab Sprig እንደ ዋቢ አድርገህ ኢትየጵያ ውስጥ እንዲደገም ቀስቅሰሃል፡፡ስለዚህም አሸባሪ ነህ፡፡
የእስክንድር የመከራከሪያ መልሶች 1-የArab Sprig በአንድም የሰሜን አፍሪካ እና የአረብ አገራት የህዝብ እንቅስቃሴ በአመፅ የመንግስት ስልጣንን ለመያዝ የተካሄደ አይደለም፤ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ እንዲካሄድ ለማድረግ እንጂ፡፡በግብፅ፣በቱኒዚያ እና በሊቢያ አንድም የፖለቲካ ፓርቲ ያለምርጫ በህዝባዊ አመፅ ስልጣን ላይ የወጣ የለም፡፡
2-የተለያዩ የአለም መንግስታት የኢትዮጵያንም መንግስት ጨምሮ ይህንን የArab Sprig እንቅስቃሴ ለፍትሕ የተደረገ ሲሉ አሞካሽተውታል፡፡ኢትዮጵያ ውስጥ አራት ጊዜ(1987፣1992፣1997 እንዲሁም 2002 ዓ.ም) ምርጫዎች ተካሂደዋል፡፡ ነገር ግን አንዱም ነፃ እናፍትሃዊ አልነበሩም፤ይህም ኢ- ህገመንግሰታዊ ነው፡፡ስለሆነም በየትኛው የሒሳብ ስሌት ነው የእኔ ይህንን የሕዝብ እንቅስቃሴ በሀገሬ እንዲደገም መፈለግ በሽብርተኝነት የሚያስፈርጀኝ?
ሌላው የአቃቢ ህግ የመከራከሪያ ነጥብ የግንቦት ሰባት አባል ነህ የሚል ነበር፡፡ለዚህም የድምፅ እና የፅሁፍ ማስረጃ አቅርቧል፡፡ እስክንድርም ሲመልስ የፅሁፍ ማስረጃውም ግንቦት ሰባት ልሳን ላይ የሚወጡት ፅሁፎች ጋር ተመሳሳይነት ስላላቸው ብቻ አባል ነህ ልባል አልችልም፡፡የድምፅ ማስረጃዎቹ ደግሞ ሁሉም በpublicly የተናገርኳቸው ናቸው(በስልክ ተጠለፈ(Interception) የተባለውንም ማስረጃ ይጨምራል)፡፡ታዲያ የት ነው በህብዑ የተንቀሳቀስኩት? አንድም እንኳ በግሌ(Private) ያደርግኩት ግንኝነት እንዴት እንደማስረጃ ማቅረብ ሳይቻል እንዴት ነው በህቡዕ ተንቀሳቅሰሃል የተባልኩት? ሲል ተከራክሯል፡፡
በተጨማሪም አቃቢ ህጉም አንተ ጋዜጠኛ ነህ ፤ ግን ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየተገናኘህ የምታደርጋቸው ድርጊቶች ከሙያህ ውጭ ሌላ የፖለቲካ አጀንዳ እንዳለህ ያሳያል በማለት ፍርድ ቤቱን ከዚህ ጋር አያይዞ እንዲያይለት ጠየቀ፡፡እስክንድርም ሲመልስ ከሁሉም ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ያደርግኩት ንግግርም ሆነ ግንኙነት ሃሳቡ ቀረበው(Initiation) ከራሳቸው ከፓሪቲዎቹ ነበር፡፡ለምሳሌ ከመኢዴፓው ዘመኑ ሞላ ጋር የተደረገው ግንኙነት ሊያካሄዱት ለታሰበው ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ የእኔ አስተያየት ለምስማት ነበር፡፡(በነገራችን ላይ ስለዚሁ ሰላማዊ ሰልፍ አስተያየት ከእኔ ብቻ አልነበረም)፡፡ እኔም በዚያ ወቅት የሰጠኃቸው አስተያየት ከቻላችሁት ሰልማዊ ሰልፉን ሰርዙት ፤ካልቻላችሁ ደግሞ ከኢትዮጵያ ውጭ ካለ ማንኛውም አካል የገንዘብም ድጋፍም ሆነ ምንም አይነት ግንኙነት አይኑራችሁ፡፡ በተመሳሳይም ሁኔታ በአንድነት ፓርቲ ላይ ያደረግሁት ንግግር በፓርቲው ተጋብዤ ነበር፡፡
ሌላው የአቃቢ ህግ ክስ ደግሞ እነ እስክንድር የሲቪክ ማህበር በማቋቋም ለሽብር አላማ ማዋል ነበር፡፡የእርሱም ምላሽ የሲቪክ ማህበሩን ልናቋቁም የነበረው ስድስት ሆነን ነበር፡፡ከነርሱም ውስጥ ሁለቱ ተከላካይ ምስክሮች ሆነውኝ ስለማህበሩ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፤ታዲያ ቀሪ አምስት የማህበሩ አባል በሽብርተኛነት ለምንስ አልተከሰሱም፤ሰዎቹም ኢትዮጵያ ውስጥ እየኖሩ ነው፡፡ታዳያ የፖሊስስ ስራው ምንድን ነው፤እነዚህን አምስት አሸባሪዎች አድኖ ያልያዘው?
Subscribe to:
Post Comments (Atom)

No comments:
Post a Comment