ሰንደቅ ጋዜጣ 8ኛ ዓመት ቁጥር 380 ረቡዕ ታህሳስ 10 ቀን 2005
በጋዜጣው ሪፖርተር
በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያለውን ብልሹ አሰራር እና ሙስና በይፋ ያጋለጡት አቶ ዳውድ መሐመድ ከኃላፊነታቸው ተነሱ።
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩት አቶ ዳውድ መሐመድ ከኃላፊነታቸው የተነሱት በሚኒስቴር መ/ቤቱ የበላይ አመራሮች ማለትም በሚኒስትሩ አሚን አብዱልቃድር እና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ታደለች ዳለቾ ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ ጉዳዩን በሰንደቅ ጋዜጣ ላይ በይፋ በመናገራቸው ተገምግመው መሆኑን ምንጮቻችን ገልፀዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የትምህርት ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ሰሞኑን በተካሄደው ግምገማ መሠረት አቶ ዳውድ ከሚኒስትር ዴኤታ ኃላፊነታቸው እንዲነሱ ሆኗል።
በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አቶ ዳውድ መሐመድ ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን የባህል ዘርፍን ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲመሩ የቆዩ ሲሆን፤ ሌላዋ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ታደለች የቱሪዝም ዘርፍን ይመራሉ።
አቶ ዳውድ በሚኒስቴር መ/ቤቱ በግልፅ የሚታየውን ሙስናና ብልሹ አሠራር በአደባባይ በመተቸታቸው ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው፣ ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለሚታገሉ ኃይሎች ሁሉ አስደንጋጭ መልዕክት ያስተላለፈ ነው ሲሉ አንድ የመ/ቤቱ ባልደረባ አስተያየታቸውን ለሰንደቅ ጋዜጣ ሰጥተዋል። “ኪራይ ሰብሳቢዎች በክብር ተቀምጠው ሕገወጥ አሠራርን የሚታገሉ ባለሥልጣን ከኃላፊነት ማንሳት ምን ማለት ነው? ለሌሎችስ የሚያስተላልፈው መልዕክት ምንድነው?” ሲሉም በአግራሞት ጠይቀዋል።
አቶ ዳውድ ህዳር 26 ቀን 2005 ዓ.ም በወጣው ሰንደቅ ጋዜጣ በመ/ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች መካከል ስለተፈጠረው ችግር ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ፤ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር አቶ አሚን አብዱልቃድር እና ሚኒስትር ዴኤታዋ ወ/ሮ ታደለች ዳለቾ ግንባር በመፍጠር በመ/ቤቱ ውስጥ ሙስናና ብልሹ አሰራር እንዲሰፍን አድርገዋል በማለት ቅሬታቸውን መግለፃቸውን፣ ይህንንም ቅሬታ ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ አሳውቀው መፍትሄ አለማግኘታቸውን በይፋ ለሕዝብ መግለፃቸው ይታወሳል። አቶ ዳውድ ለሰንደቅ ሰጥተውት ከነበረው መግለጫ የተወሰነውን ክፍል እነሆ በድጋሚ አትመነዋል።

*** **** ***
“አንድ ችግር በግልፅ ካልወጣ ወደ እቅድ መግባት አይቻልም” የሚሉት አቶ ዳውድ ሰራተኛው የሚጋራቸው በርካታ ችግሮች እንዳሉም ጠቅሰዋል። ሰራተኛውን ሚኒስትሩ እና ሚኒስትር ዴኤታዋ (ወ/ሮ ታደለች) በኔትወርክ በመያያዛቸው መካከለኛ ማኔጅመንቱ እንዲጠናከር አልፈለጉም ሲሉ ቅሬታቸውን የገለፁት አቶ ዳውድ፤ “ካለን ወደ አንድ ሺ ስምንት መቶ ሰራተኛ ውስጥ የተወሰነ ሃያ ወይ ሰላሳ ሰው ይዞ መሄድ ምን ያህል አግባብ ነው ለሀገርስ ይጠቅማል” ሲሉ ጠይቀዋል። ሚኒስትር ዴኤታው፤ ሚኒስትሩ አቶ አሚን እና ሌላኛዋ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ታደለች “የተወሰነ የራሳቸውን የጥቅም ኔትወርክ ይዘዋል” ሲሉ አጋልጠዋል። ወ/ሮ ታደለች የሚኒስትር መስሪያ ቤቱን ማርኬቲንግ ክፍልና የሚኒስትሩ አማካሪ በመያዝ የማይሆኑ ሰዎችን በማሰባሰብ ለውጥ ማምጣትም አይችሉም ብለዋል።
“በቱሪዝም በኩል በጣም የሚያሳዝነው በሰኔ 2006 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩም በሚያውቁት ኮሚቴ ተቋቁሞ ዝርዝር የሆነ የቱሪዝም ዘርፍ ልማት ስትራቴጂ ወጥቶ ነበር። እኛ ግን ከመጣን ሁለት ዓመት ሊሞላን ነው። ወ/ሮ ታደለች ደግሞ ለሰባት ዓመት በቦታው ቆይታለች። ነገር ግን የተጠናውን ጥናት ተግባራዊ ማድረግ አትፈልግም። አቅሙ የላትም። ሌሎች አገሮች ይህ ስትራቴጂ አላቸው። ለምሳሌ ደቡብ አፍሪካ ቱሪዝም ሴክተር ዲቪሎፕመንት ስትራቴጂ አላቸው። በእኛም በኩል ስትራቴጂው ያስፈልገናል። ቱሪዝም ሳተላይት አካውንት በሚባለው አሰራር ስንት ቱሪስት መጣ፣ ምን ያህል ወጪ አወጣ፣ ወዘተ የሚል መረጃ የለንም ብቻ ሳይሆን፤ ለማወቅም ፍላጎት የላቸውም። በየወሩ ወደ ሲቪል ሰርቪስ ሲላክ ተገምግሞ ቢሆንም ይህንንም የመፈፀም ፍላጎት የላቸውም” ሲሉ ጠቅሰዋል።
በሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ውስጥ ሙስናና ብልሹ አሰራር መኖሩን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው “ለምሳሌ ሚኒስትሩ 128 ሺህ ብር ከመስሪያ ቤቱ ሂሳብ ቋት ወጪ በማውጣት ለህክምና ተጠቅሟል። በመመሪያው መሰረት ሚኒስትሮችና ሚኒስትር ደኤታዎች ስንታመም መታከም ያለብን ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ነበር። ነገር ግን ከባህልና ቱሪዝም ፋይናንስ ወጪ በማድረግ በወ/ሮ ታደለች በተፈረመ ወጪ አላግባብ ታክመዋል” ብለዋል። ይህ ብልሹ አሰራር ማስረጃ ያለው በመሆኑ እንጂ ማስረጃ የሌላቸው በርካታ ብልሹ አሰራር በተቋሙ ውስጥ መኖሩን ጠቁመዋል።
በወ/ሮ ታደለች ስር የ35 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት መኖሩንም የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው ይህ ፕሮጀክት እየተጓተተ መሆኑንም ተናግረዋል።
“ከሁሉም እኔ የሚያስጠላኝ ለቋሚ ኮሚቴ የሚቀርበው ሪፖርት ውሸት ነው። ሲቪል ሰርቪስ የሚቀርበው ሪፖርት ውሸት ነው። እኛም ጋ ማኔጅመንት ስንገማገም የሚቀርበው ሪፖርት ውሸት ነው። እኔም ውሸት ሲሰለቸኝ ተውኳቸው”ሲሉ የተማረሩት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ቀደም ሲል ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሰው ተመድቦ ለአንድ ቀን በር ዘግተው ተገማግመው እንደነበር አስታውሰዋል። በዛን ጊዜ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ችግሩን እንድንፈታ አቅጣጫ ተቀምጦ ፍቱ ተብሎ እንደነበር ጠቅሰው ሚኒስትሩን ወ/ሮ ታደለች አቅጣጫውን አልተቀበሉትም። ምክንያቱም ወደ ትክክለኛ አቅጣጫ ከሄዱ ተጠቃሚነትን ያጣሉ። በዚህም መሰረት የተሳሳተውን አቅጣጫ ማስቀጠል ነው የመረጡት ብለዋል።
“ከእኛ በፊት የነበሩ ሚኒስትሮች ፎቅና ቤት ሲሰሩ በማየታቸው እነሱም መስራት ይፈልጋሉ። ስለዚህ ይሄንን ለመፈፀም የተሳሳተ አቅጣጫ መከተል አለብህ ትክክለኛና ህዝባዊ አቅጣጫ ሳትከተል ግን አታገኝም” ሲሉ አያይዘው ገልፀዋል።
አቶ ዳውድ መሐመድ ቀደም ሲል የሶማሌ ክልልን በፕሬዝዳንትነት የመሩ ሲሆን፤ በዚህ የሥልጣን ዘመናቸውም በጅጅጋ አካባቢ በሕገወጥ መንገድ በስፋት የሚዘዋወረውን ጫት ሕጋዊ መስመር እንዲከተል መወሰናቸውን ተከትሎ የጅጅጋ ነዋሪዎች በዚያው አካባቢ የሚበቅል ጫት ለመጠቀም ተገደዋል። ይህንንም ጫት “ዳውድ” በማለት ስያሜ የሰጡት ሲሆን፤ እስካሁንም ድረስ በጅጅጋ አካባቢ “ዳውድ ጫት” የሚታወቅ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልፀውልናል።

No comments:
Post a Comment