FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Wednesday, January 16, 2013

የአለም ባንክ በኢትዮጵያ የሚታየው የሙስና ደረጃ እያደገ መምጣቱን ይፋ አደረገ


ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የአለም ባንክ በኢትዮጵያ የሚታየው የሙስና ደረጃ እያደገ መምጣቱን ይፋ አደረገ:: በተለይ የቴሌኮም ዘርፉ ለከፍተኛ  ሙስና የተጋለጠ መሆኑን አስታወቀ::
ባለፈው አርብ በአለም ባንክ ይፋ የተደረገ ሪፓርት እንዳመለከተው በተለይ በግዥና በአቅርቦት ሂደቶች የሚታዩት ክፍተቶች ለሙስና አደጋ በመጋለጥ ከፍተኛውን ድርሻ መያዛቸውን ሪፓርቱ አመልክቷል::
የሀገሪቱን የሙስና መጠን ላለፉት ስድስት ወራት ሲያጠና የቆየው የአለም ባንክ በተለይ አዳዲስ የኢንቨስትመንት መስኮች ብሎ በመደባቸው ንዑሳን ክፍሎች ውስጥ የተካተቱት ቴሌኮም፣ የኤች አይ ቪ መከላከልና ህክምና የመድሀኒት ዘርፉን ጨምሮ በሙስና ቀለበት ውስጥ የወደቁ ናቸው ብሏል::
በመሰረታዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ብሎ ባንኩ በመደባቸው ትምህርት፣ ጤና፣ ፍትህና የመሳሰሉት ተቋማት ቀላል የማይባል ሙስና የሚታይባቸው መሆኑን አጋልጧል::
ባንኩ ያፋ ባደረገው በዚህ ሪፓርት ከፍተኛ ሙስና ከሚታይበት ከቴሌኮም ኢንዱስትሪ ቀጥሎ መሬትና ኮንስትራክሽን ዘርፉ በሙስና መዘፈቁን ይፋ አድርጓል::

No comments:

Post a Comment